ሸክም ይሰማሃል ወይ ክርስቲያን ወንድሜ ሆይ?
ለሚጠፉት ወገኖች ልብህ ያዝንብሃል ወይ?
ጥፋታቸው ተሰምቶህ አዝነህ ትጸልያለህ?
በራስህ ተመክተህ ወይንስ በመፍረድ ላይ ነህ?
1.
በሞት ጐዳና ላይ ሆነው ወደ ሞት ሲያዘግሙ
ልብህስ ያዝንብሃል ወይ ይሰማሃል ወይ ሸክሙ።
2.
አንተስ በመጀመሪያ የት ነበርክ ከየት መጣህ?
በከንቱ ስትሮጥ ስትባዝን ኢየሱስ ነው ያወጣህ
3.
ጌታ እንደ ሞተላቸው ስለ እነርሱ ተጐድቶ
አንተ ዝም ካልክ ወንድሜ ማን ይናገራል ከቶ።
4.
ፍቅር የተሞላ መልእክት ፍቅር ከአምላክ ከላይ
ኢየሱስ እንደሚያድን መናገር አትችልም ወይ
5.
ስለ ጌታ እንመስክር እንናገር ስለ እርሱም
በመጨረሻውም ጊዜ ያለ ዋጋ አይተወንም።