1.
በዚች በዕድሜ ዘመን ስኖር ከኢየሱስ ጋር
ብዙ የሚያስደስት የሚያሳዝን ነገር
አየሁ በዐይኖቼ በጆሮቼም ሰማሁ
በፀጋው አቁሞኝ ዕድል ስላገኘሁ
ምሥጋና ምሥጋና (2)
ላቅርብ ለጌታዬ እንደገና
2.
ሕይወት ለዛ አጥቶ ዓለም ስትከፋፋ
ክህደት ተንሰራፍቶ አምላክ ባይ ሲጠፋ
ኢየሱስ ጌታ ነው ለማለት ላበቃኝ
ምሥጋና ውዳሴ ይድረስ እላለሁኝ
3.
ያለፈውን ዘመን በደሃና አሳልፎ
ለሚመጣው ደግሞ በክንዱ ደግፎ
የሚያቆመኝ ወዳጁ ጓደኛ ስላለኝ
ምሥጋና ማቅረቡ እንዴት ይነስብኝ