ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #80d / Song #80d

አምላኬ ያዳረገውን ነገር

English Translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: Unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
አምላኬ ያዳረገውን ነገር
ሁሉ ባወራው ባወራው ባወራው ባወራው
ከቁጥር ሁሉ በዛ ተዓምራቱ
ብዙ ነው ባወራው ( 2)
1.
ኃጢአተኛ ከፍ ከፍ ብሎ አይቼ
እንደ ሊባኖስ ዛፍ ለምልሞ ፈርቼ
ተመልሼ ከቦታው ፈለግሁት
እንኳን እርሱን ስፍራውን አጣሁት
2.
የክፉ ኃይል በቁጣ ዓይኖቼ እያየኝ
ጥርሱን በላዬ ላይ ስያንገጫግጭብኝ
እግዚአብሔር ግን አይቶ ስቆበታል
የመጥፍያው ቀን እንደደረሰ አውቋል
3.
ከመቅደሱ ከሰማይ ከፍታ ላይ ሆኗል
ወደ ምድር በታች አሽቆልቁሎ አይቷል
የእስረኞቹን የጩኸት ቃል ሰምቷል
ከሞት አፋፍ ከፍርድ ወጥመድ ፈቷል
4.
ከሰይጣን ኃይል የዳናችሁ ሁሉ ከሰይፉ
ለሚመጣው ትውልድ ጻፉና አስተላልፉ
አምላካችን ይህን ተአምር ሰርቷል
እኔም ባወራ ባወራው በዝቷል
100%
100%