ደግመህ ደግመህ ባርከን አሁንም (2)
እረክተናል ጠግበናል አንልም (2)
ጽዮን ስንደርስ ብቻ ነው እርካታችን (2)
እስከዚያው ግን መግበን አባታችን
1.
ደግመህ ደግመህ መግበን ቃልህን (2)
በኛም ዘመን ግለጸው ኃይልህን (2)
እንመልከት ስትሠራ በፊታችን (2)
ኃይሉ ይቅለጥ ይሰበር ጠላታችን
2.
ደግመህ ደግመህ አሰማን ድምጽን (2)
ፍጻሜያችን ያማረ እንዲሆን (2)
ከእውነትህ እንዳንስት በጉዟችን (2)
ሕያው ቃልህ ይሁነን ምርኩዛችን
3.
ደግመህ ደግመህ አሳየን ክብርህን (2)
ከእሳት ከውኃ አድነን ሕዝብህን (2)
ከእኛ ጋር እንዳለህ በዓለም ይታይ
አንተም ክበር ከፍ በል በምድር ላይ (2)