1.
ማዕበሉ ሳይጥሰኝ ውሃውም ሳያሰጥመኝ
እጄን በእጁ ይዞ ወንዙን አሻገረኝ
የፈተናው እሳት ወላፈን ሳይጎዳኝ
በጌታዬ ጸጋ በሕይወት አለርፍኩኝ።
ባለፍኩበት መንገድ ለኔ ተጠንቅቆ
እዚህ አደረሰኝ ከክፉ ጠብቆ
እስከ ፍጻሜውም ያቆመኛል ጌታ
አገሬ ገባለሁ እምነቴ ሳይፈታ።
2.
ከህያዋን ጋር ኖሬ እንዳከብርህ
መከራን አልፌ እንዳመሰግንህ
ኢየሱስ ከጎኔ ቆሞ አበረታኝ
ከአንበሳ አፍም ደጋግሞ አወጣኝ።
3.
ሕይወቴን ለአምላኬ አደራ እየሰጠሁ
በእረኛነቱ ሥር ሳልሰጋ እኖራለሁ
ከክንፎቹ በታች እተማመናለሁ
በእርሱ ተጠብቄ ሐገሬ እገባለሁ።
4.
ጌታ የሠራውን ድንቅ አስታውሳለሁ
ስላለፈው ዘመን አመሰግናለሁ
ከፊቴ ላለውም በእርሱ እደገፋለሁ
በዘላለም ክንዱ በእቅፉ እኖራለሁ።