ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #96d / Song #96d

የድል መንገድ ነው ይህ ጉዞዬ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
የድል መንገድ ነው ይህ ጉዞዬ
ማንም አይለየኝም ከጌታዬ
1.
የዓለምን ነገር ድል ነስቻለሁ
ሁሉን ትቼ ልጅህ ሆኛለሁ
ከእንግዲህ ወዲህ አልመለስም
ለዓለም ሥራዎች አልሸነፍም
አልሸነፍም ጌታን አልተወውም።
2.
ብገፋ በምድር እጠባበቃለሁ
ልጁ ስለ ሆንኩ እወርሳታለሁ
በደስታ በምድር በጽዮን አገር
እኖራለሁ በመዘመር
በመዘመር ከበጉ ጋር።
3.
በጉን ሳወድስ በዝማሬ
ከቅዱሳን ጋር እኔም አብሬ
አይረባኝ አልጨነቅ
ልጁ ስለ ሆንኩ አልጠማም
ድል እነሣለሁ የሥጋን ነገር።
4.
ክርስቲያን ወንድም ያለህ በምድር
ጽዮን አለልህ የተስፋ አገር
በድል መንገድ ላይ ድል ትነሣለህ
ለዘላለም ቅዱሱን ታያለህ
እልል ትላለህ ከአባትህ ጋር ነህ።
100%
100%