1.
ትውስ ሲለኝ የጌታዬ ፍቅር
ያደረገልኝ በጐልጐታ
ከአገር ወደአገር በመንከራተት
ፀሐይና ውርጭ ሲፈራረቅበት
ይሁዳ ሸጦት ጴጥሮስ ሲከዳው
ተከታዮቹም ጥለውት ሲሸሹ
የፍጥኝ ታስሮ ለፍርድ ሲነዳ
ጥፊውና ግርፉ ሲወርድበት
ትዝ ይለኛል ያ መድህኔ
በእንጨት ላይ የሞተው ስለእኔ
ትውስ ይለኛል የመስቀል ፍቅሩ
ያደረገልኝ ውለታ ሁሉ
2.
አልራሩለትም አስረው ሲገርፉት
ያን መልክ መልካም ሩህሩህ ፈጣሪ
የማይችለውን መስቀል አስይዘው
መድህናቸውን ለፍርድ ሲወስዱት
ሲጮህ ሲያነባ በጣር ተከቦ
በደም ላይ ባሕር ሆኖ ሲያነባ
ሲወድቅ ሲነሳ አባ አባት ሲል
ተሰቃየልኝ ነፍሱ እስክትዝል
3.
ይረሳኛል ወይ ያ የጣር ጊዜ
መድሃኒቴን የተሳለቁበት
ከመስቀል ቅረድ ራሽን አድን
እያሉ ጠላቶቹ ሲያሾፉበት
ጨለማ ውጦን የነበረውን
እኛን ለማዳን ከክብሩ ወርዶ
የዓለምን ኃጢአት ያስወገደውን
ታላቁን መድህን ነፍሴ አትረሳውም