ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #172d / Song #172d

በዚህ ሁሉ ዘመን ኢየሱስ ጌታ ነው

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: ዘማሪ ታምራት ኃይሌ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 4
1.
አይቸኩልም ጌታ አርፍዶ ይነሳል
ግን ማንም አይቀድመውም
በጊዜው ይደርሳል
ጌታን ከዙፋኑ ለማውረድ የለፉ
ትላንት የነበሩ ዛሬ ግን የጠፉ
እጅግ ብዙ ብዙ ናቸው
ታዲያ ምን ያደርጋል ሞት አሸነፋቸው።
በዚህ ሁሉ ዘመን ኢየሱስ ጌታ ነው
ትላንትናም ዛሬ ለዘለዓለም ያው ነው (2x)
2.
መቃብር ጠባቂው በከንቱ ሲጉላላ
ኢየሱስ ተነስቶ ከተማውን ሞላ
ዛሬም ባዶ ህንጻ ሰይጣን ያስጠብቃል
ጌታ የጓዳውን ህዝቡን ያነቃቃል
ግሩም ነው ድንቅ ነው
ዛሬም ለዘለዓለም ኢየሱስ ጌታ ነው።
3.
ነብያት ነን ባዮች በስሙ የነገዱ
የአምልኮ ምልክ ይዘው ኃይሉን ግን የካዱ
ስተው እያሳቱ ጥቂት ዘመን ኖሩ
ቀናቸው አበቃ ሞቱ ተቀበሩ
አለ በአፈር አጥንታቸው
በጐልጐታ ያለው ባዶ መቃብር ነው።
4.
እውነት መሰል ተረት ይዘው የተነሱ
በወሬ መሰላል ሰማይ የደረሱ
ፈጣሪ አማልክት መባል ያማራቸው
ከነፋቄያቸው ጋር ምድር ዋጠቻቸው
ተረታቸው ወዴት አለ እውነተኛ አምላክ
ኢየሱስ ነው ተባለ።
100%
100%