ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #178d / Song #178d

ኃይለኛ እንዳንተ የለም

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
1.
ከባርነት አገር ወደ አንተ ያመጣኸን
ቀንበርን ሰባብረህ አርነት ያወጣኸን
በጨለማ ያለ ህዝብ ታላቅ ብርሃን አየ
ከሰቆቃ ኑሮ ከሳይጣን ተለየ
ኃይለኛ እንዳንተ የለም
ንገሥ ዘለዓለም
ማህተሙን ኧረ ማን ፈታ
ከፍ በል ጌታ (2)
2.
እግዚአብሔር ኃያል ነህ ማንንም አትንቅም
የሚጤሰውን ጧፍ አጥፍተህ አታውቅም
ለደካማው ኃይልን ለጭንጋፉ ሞገስ
አንተ ግን ጌታ ነህ ለዘለዓለም ንገሥ
3.
በሰማይ በምድር ከምድር በታች ሁሉ
ማኅተሙን ሊፈቱ አንዳቸውም አልቻሉ
የነገሥታት ንጉሥ የጌቶቹ ጌታ
አንተ ግን ችለሃል ማኅተሙን ልትፈታ
4.
ሞተሃል ተብሎ እኛም ተስፋ ቆርጠን
በራችንን ዘግተን አዝነን ተቀምጠን
አንተ ግን ልዩ ነህ ታሪክ ለውጠሃል
ሞትና መውጊያውን ለዘለዓለም ሰብረሃል
5.
ትዕቢተኛውን ፈርዖን ሊያጠፋን ሲነሳ
ዙሪያችንን ሲዞር ሊውጠን እንደ አንበሳ
ቀድመህ ደረስክና አፉን ለጐምክልን
ምን እንበላ ሌላ ለእኛስ ዘለዓለም ንገሥልን
100%
100%