ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #23h / Song #23h

ዳንኩኝ

Redeemed

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
1.
መዳኔን ላውጅ እወዳለሁ
በሞተው በግ ደም ድኛለሁ
ወሰን በሌለው ምህረት ዳንኩኝ
ለዘላለምም ልጁ ነኝ
ዳንኩኝ ዳንኩኝ
በሞተ በግ ደም ድኛለሁ
ዳንኩኝ ዳንኩኝ
ለዘላለምም ልጁ ነኝ
2.
ዳንኩኝ በየሱስ ደስታ አለኝ
ቋንቋ ሊነግረው የማይችል
አውቃለሁ የጌታዬ ብርሃን
ዘወትር ከኔ ጋር ይኖራል
3.
ብሩክ አዳኜን አስባለሁ
እርሱን ሳስብ እውላለሁ
ያለ እረፍትም እዘምራለሁ
ፍቅሩም የመዝሙር
ዜማ ነው
4.
ሕጉ የሚያረካኝን ንጉሥ
በክብር እንዳየው አውቃለሁ
በፍቅሩም ነፍሴን ይጠብቃል
መዝሙር በሌት ይሰጠኛል
5.
ዘውድ እንደሚቆየኝ አውቃለሁ
በዚያ በሚያበራው ሥፍራ
ፍጹም ከሆነው መንፈስ ጋራ
በጌታ ቤት እኖራለሁ
100%
100%