1.
ሁሉን የፈጠረ
አምላክ ይመስገን
ዓለምን ወዶ
ልጅን እስኪሰጠን
ከኃጢዓት ሊያነጻን
ሕይወቱን ሰጠን
የሕይወት መንገድ
ደግሞ ከፈተልን
ተመስገን ተመስገን
ምድር ሁሉ ስሙት
ተመስገን ተመስገን
ሰው ሁሉ ይደሰት
በልጁ የሱስ
ወደ አብ እንድረስ
ሁሉን ለፈጠረ
ምስጋና ይድረስ
2.
ኦ ፍጹም ደህንነት
በደም የገዛን
ለአማኙ ሁሉ
ተስፋ የሰጠን
የበደለ ሁሉ
በውነት ቢያምን
በዚያችው ሰዓት
ያገኛል ይቅርታን
3.
እርሱ አስተማረን
እርሱ ፈጠረን
በልጁ በየሱስ
እጅግ ደስ አለን
ከዚህ ሁሉ በላይ
እንነጻለን
የሱስን እያየን
እንጓዛለን