ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #74 / Song #74

ለወደደን ለእግዚአብሔር ምስጋና x2

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
ለመሃሪው አምላካችን ምስጋና x2
ለሚረዳን ለእግዚአብሔር ምስጋና x2
ለታደገን አምላካችን ምስጋና
1.
አሜን ምስጋና ይሁን ለጌታ
በታላቅ ኃይሉ ሁሉን ለረታ
ኤልሻዳይ ጌታ
2.
ለታጋሹ አምላካችን ምስጋና x2
ምህረቱን ላበዛልን ምስጋና x2
ከወደቅንበት ላነሳን ምስጋና x2
በፀጋው አቅፎ ላቆመን ምስጋና
3.
ወጥመዱን ለሰበረልን ምስጋና x2
ከጠላት ኃይል ለታደገን ምስጋና x2
መከታችን ለሆነልን ምስጋና x2
አሳልፎ ለማይሰጠን ምስጋና
4.
ችግራኛውን ለሚያስበው ምስጋና x2
ከትቢያ ላይ ለሚያነሳው ምስጋና x2
በከፍታው ለሚያኖረው ምስጋና x2
እንሰዋለን ለእግዚአብሔር ምስጋና
5.
ለሞተልን አምላካችን ምስጋና x2
ለቀደሰን አምላካችን ምስጋና x2
ላሳደገን አምላካችን ምስጋና x2
ባባቱ ቀኝ ላስቀመጠን ምስጋና
100%
100%