ባማረ ቅኔ ለኢየሱስ ምሥጋና
ቃሉን የሚያደርግ ድንቅ አምላክ ነውና
ደመናም ባላይ ሸለቆው ይሞላል
ሰው የማይችለው ለእግዚአብሔር ይቻላል
1.
እኔስ ተስፋ አልቆርጥም ፍፁም አላፍርም ባዳነኝ ጌታ
አይቻለሁና በዐይኔ ያስጨነቀኝን ሲመታ
ነገር ባይሞላ ባይሳካ ኢየሱስ ምን ይሳነዋል
ከሞተው አንበሳ ሆድ ውስጥ ጣፋጭ ጣፋጭ ማር ያወጣል (፪x)
2.
ለምን ልጐሳቆል ልዘን ለምንስ ልቆዝም በእንባ
ተዓምር ያስለመደኝ አምላክ መቼ ክንዱ ደከመና
በታሰርኩበት ወህኒ ውስጥ ሆ እያልኩኝ እዘምራለሁ
የጠላቶቼን ደጅ በእምነት በዝማሬ አፈርሳለሁ (፪x)
3.
ውድቀቴን ጠላቴ ሰምቶ ከበሮ ተይዞ ሲጨፈር
አምላኩ ጥሎታል ዛሬስ ተብሎ አዋጅ ሲነገር
ሰው የማይጥል ጌታ አምላኬ ኃያል ክንዱን ሲዘረጋ
ጠላቶቼ ሁሉ አለቁ
በአንዲት የአህያ መንጋጋ (፪x)
4.
ሰላሙን ሞልቶ አባቴ በመስቀሉ ስራ አሳረፈኝ
ወደ ክብሩ ልጁም መንግሥት በታላቅ ፍቅሩ አፈለሰኝ
ልጁን ለእኔ የሰጠ አምላክ ሌላ ምን ምን ይሳነዋል
ባዶ ሸለቆዬ ሞልቶ ተርፎ ለአገር ሁሉ ይፈሳል (፪x)