ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #182d / Song #182d

በመጠበቁያዬ ላይ ሆኜ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 5
በመጠበቁያዬ ላይ ሆኜ
አየዋለሁ አይኒን አሻቅቤ
አልሄድም አማራጭ ፍለጋ
አምናለሁ መልስ አለ እሱ ጋ
1.
ወደዚህ ወደዚያ አይኔን አላነሳም
ፈጥጌኔም ቸኩዬም አቋርጭ አልሄድም
ዝምብዬ ብቻ እሱን ጠብቃለሁ
ነገሬን በሙሉ ለሱ አሳየዋለሁ
አምናለሁ አምላኬ እንደማጎበኘኝ
ፀሎቴን መልሶ እንደሚያስሰደንቀኝ
2.
የማይሆን ቢመስልም የማይሳካልኝ
እንደመሸ ሚቀር ቀን የማይወጣልኝ
ቢሆንም አምላኬን እጠብቀዋለሁ
መድሃኒቴ እሱ ነው ተስፋ አደርገዋለሁ
አንዴ ሰማያትን ያንጎዳጉድና
ፅዋዬን ይሞላል ኤልሻዳይ ነውና
3.
እስክመቼ ድረስ እያልኩ በልቤ
አላማርረውም በጭራሽ አምላኬን
እሱ ለሄ ብሎ ሳይደክም ሲተጋ
በጭራሽ አልሄድም አማራጭ ፍለጋ
የሚቀር ይቅር እንጂ ሌላ ምን ይመጣል
ኢየሱስ ብቻውን እሱ ይበቃኛል
4.
ሁልጊዜ በጌታ ደስ ደስ እያለኝ
አመልካለሁ እንጂ ምን ክፉ አናገረኝ
የሚሆነው ሆኖ ማለፍ ለማይቀር
ለምን በአምላኬ ሳይ አምርሬ ልናገር
የገባልኝ ተስፋ ቢመስል የዘገየ
ዩከብራል ጌታ ጠላት በይኑ እያየ
100%
100%