ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #51 / Song #51

እንለምንሃለን በፊትህ ተንበርክከን

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
እንማፀንሃለን በአንድ ላይ ሆነን
መንፈስህ ከኛ ጋራ ሥራውን እንዲሰራ
እንማፀንሃለን
1.
ምፃትህ መቃረቡን ለዓለም እናውጅ
ጌታ ሆይ በመንፈስህ አድሰን እንዘጋጅ
የመገለጽህ ጊዜ በደጅህ መሆኑን
ይህንን ላላወቁት እንናገር አሁን
2.
የምሥራቹን ቃል ለሁሉም እናዳርስ
በተለወጠ ሕይወት ቤትህን እናድስ
ለሥራህ እንቅና መንፈስህ ይደርብን
ከእንግዲህ ይበቃናል ለሥጋ መባከን
3.
ሩጫችንን ጨርሰን አክሊል ለመሸለም
በቃል በኑሮአችን ተለይተን ከአለም
አንተን እናክብርህ ዘወትር በኑሮአችን
እኛም ተለውጠን እንለወጥ ሌሎችን
4.
ለሌሎች መስክረን እኛ እንዳንጠፋ
በዚያ በታላቅ ቀን እንዲኖረን ተስፋ
በትንሳኤ ማለዳ ከቀኝህ እንድንሆን
በመንፈስህ ሙላን አድሰን ልባችንን
100%
100%