ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #164d / Song #164d

ተመስገን ተመስገን

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
1.
የእግዚአብሔር ምህረቱ ብዙ
ደካሞችንም ማገዙ
በጀርባው አዝሎ መሸከሙ
ከኃጢአት ማንጻት በደሙ (2x)
ተመስገን ተመስገን ተመስገን ጌታ ሆይ
ለዚህ ያደረስከኝ አንተ አይደለህም ወይ (2x)
2.
እኔስ አይቻለሁኝ ፍቅሩን
ከፋንድያ ላይ ማንሳቱን
ዛሬ ሰው ሆኜ እዘምራለሁ
ለዚህ ክብር በቅቻለሁ (2x)
3.
እጅግ ተንቄ በሰው ዘንድ
ተጥዬ ነበር በአመድ
ግን ጌታ ኢየሱስ ፈልጐኝ
ከኃጢአት/ከጅግር ማጥ ውስጥ አወጣኝ (2x)
4.
አይገርማችሁም ወይ ወገኖች
የልዑል አምላክ ባሪያዎች
ተነሱ ዘምሩ ለጌታ
እጅግ ብዙ ነው ውለታው (2x)
100%
100%