1.
በራሴ አልመካም ጉድለቴ ብዙ ነው (2)
ሰው ከራሱ የሆነ ምን በጐነት አለው (2)
መንፈስ ግን ሲመጣ በኃይሉ ሲያግዘኝ
ጠላቴን እረታለሁ ያን ጊዜ ብርቱ ነኝ (2)
ከድካሜ በቀር ስለራሴ የለኝም የማውቀው
ማን መንፈስህ በእኔ ላይ እጅግ ኃይለኛ ነው
2.
ጌታ ከደካማው ከትል ጋር ይቆማል (2)
ታላቁን ተራራ በፊቱ ይንዳል (2)
ያንተ መንፈስ በእኔ ላይ እንዳለ ሲሰማኝ
ማንነቴን ረሳሁ ኩራት ኩራት አለኝ (2)
3.
ማን መስዬሃለሁ በፊቴ የፎከርከው (2)
ጐልያድ ግዙፍ ሰው ግን ባዶ ቀፎ ነህ (2)
ምንም ታናሽ ብመስል ላልተገረዘ ዐይንህ
ወንጭፌ አይደለም ጌታ ነው የጣለህ (2)
4.
ደካማ መሆኔን ምንም ውስጤ ቢያውቀው (2)
እመካበታለሁ ድካሜ ኃይሌ ነው (2)
እኔ ልስማማ እንጂ ከመንፈሱ ጋራ
ከባሕር ይወድቃል ተነድሎ ተራራው (2)