ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #31 / Song #31

እምነት ነው የሚያድነን

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ተስፋ ነው የሚያፀናን
ፍቅር ነው የሚጠቅመን
ለአምላክ መንግሥት የሚያበቃን
1.
አብረሃምም አምኖ ፀደቀ
የሀይማኖትም አባት ሆነ
እምነቴን አፅንቼ ልጠብቅ
ጌታ በክብር እስኪገለጽ
2.
እዮብ አምላኩን ተስፋ አረገ
በትዕግሥቱም ፀንቶ ቆመ
እኔም አምላኬን ተስፋ ላርገው
የርሱ መገለፅ በድንገት ነው
3.
አፍቃሪ አምላክ እኔን ወዶ
ለኔ ለጠላቱ ተዋርዶ
አፍቅሮኛልና እኔም ላፍቅር
በጌታዬ ቤት ሁሌ እንድኖር
4.
እምነት ይኑረን በሕይወታችን
ተስፋ አንቁረጥ በጉዞአችን
ፍቅራችን ይጠንክር የሁላችን
የሰማይ አምላክ እንዲባርከን
100%
100%