ቅዱስ ነህ ዛሬ አይቻለሁ
አህዛብ በሙሉ ስማኝ
የየሱስ ፍቅር ግድ አለኝ
1.
ላክብረው የኔን ጌታ
ተወደስ ጠዋት ማታ
ላንግስህ በዝማሬ
ኢየሱስ ጌጤ ክብሬ /2/
2.
በዘንዶ ራስ ላይ እቆማለሁ
ጠላቴን አሸንፋለሁ
አክሊሌን እቀዳጃለሁ
ኢየሱስ ክበር እላለሁ
3.
አፌንም ዛሬ እከፍታለሁ
ክብርህን በዐይኔ አይቻለሁ
ላልሰሙት ሁሉ አሰማለሁ
የሱስ ሆይ ልጅህ ሆኛለሁ
4.
ላክብረው የኔን ጌታ
ተወደስ ጠዋት ማታ
ምስጋና ይገባሃል
በደምህ ዋጅተኸኛል /2/
5.
ከሰማይ መናን ያዘንባል
ደኸውን አሱ ይመግባል
በስሙ ለታመነበት
ያገኛል የምድር በረከት