ድል በድል እንሄዳለን
በአምላካችን ቅጥር እየዘለልን
ከኃይል ወደ ኃይል እየዘለቅን
ጌታችን ነግሶ እናየዋለን
1.
አውሎ ነፋስ ተነስቶ ብዙ ቢፈትነንም
ካለንበት መሠረት ሊነቅለን ቢገፋንም
በጥልቁ ከተተከልን አያነቃንቀንም
የማዕበል ሁሉ አዛዥ ለእድቀት አይሰጠንም
2.
ቸነፈር ረሃብና የችግር መፈራረቅ
ዘማዊ ትውልድ በዝቶ ኑሮ ቢሆን ትንቅንቅ
ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ በእምነት አድረን
ከኃጢአት መዘዝ ተርፈን ድልን እናውጃለን
3.
ጦርና የጦር ወሬ ሰምተን ተደናግጠናል
በደም መፍሰስ ምክንያት እጅግ በጣም አዝነናል
ሆኖም በጸሎት ተግተን ጌታን ተነስ ብንለው
ቶሎ ይደርስልናል እርሱ የቅርብ አምላክ ነው
4.
ያቃተን ነገር ሁሉ ከእግሮቻችን ሥር ወድቆ
ጠላት ያቆጠቆጠው በኢየሱስ ሥም ደርቆ
በምድር ዙሪያ ሁሉ የወንጌል እውነት ገኖ
ገና እናየዋለን እግዚአሔር ታላቅ ሆኖ