ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #61 / Song #61

ምህረት ምህረት ሰላም በዝቶ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
በላይ በሰማይ ተንሰራፍቶ
ተቀምጧል ሰላም ሰጪው
ይመለሳል ድል አድራጊው
1.
ለጠበቀና ምህረት ለሚሻው
እንደፈቃዱ ሆኖ ለሄደው
ሥፍራ ይኖራዋል በሰማይ ቦታ
ከዚያም ይኖራል በጥሩ እርካታ
2.
የያዕቆብ በመከረ ስደቱ ሁሉ
ኦ እንዴት ያስፈራል ሲታይ በቃሉ
ነገር ግን እሱ ሀይል ነው ጌታ
ያሳልፈናል የማታ የማታ
3.
ዘመኑን አይቶ ለሚጠነቀቅ
የትንቢቱን ቃል ለሚጠብቅ
ጌታ ያቆማል በምህረቱ
ደግሞ ይወስደዋል ወደ አባቱ
4.
እፎይታ ሰላም ያስፈልገናል
በመንፈስ ማረፍ ዛሬ ሽተናል
ባምልኮታችን መስመር ሠርተናል
ጌታ የሱስ ሆይ ጐብኘን ብለናል
100%
100%