አፅናኙን ላክልን መንፈስህን
ጌታ ሆይ አስበን ህዝብህን
አንዴ ጐብኘን ልጆችህን
1.
ብዙ ሮጠናል ነፍሳትን ለመመለስ
እጅግም ለፍተናል ሥራህን ለመጨረስ
ነገር ግን ለካስ ያለ መንፈስህ
ሥራህ አያልቅም ጐብኘን በኃይልህ
2.
ማነስም አይደለም ወይ በቁጥር መብዛት
በጉልበት አይደለም ወይም በብርታት
በመንፈስህ እንጂ ሥራህን መሥራት
አቤቱ አስበን በመንፈስህ ሙላት
3.
እጅግ ተንከራተናል ለብዙ ዘመናት
እንዳለፉት እስራኤሎች እምነትን በማጣት
ከእንግዲህ ይብቃን ያለ አንተ መሥራት
መንፈስህን ስጠን የሰማዩ አባት
4.
ከክብርህ የተነሳ ምድር እንድትበራ
በኛ ሆኖ ሥራህን በኃይል የሚሠራ
መንፈስህ እጅግ ያስፈልገናል
አስበን የሱስ ኃይልህ ያሻናል
5.
ሥራህን ጨርሰን መንፈስ ቅዱስ ወርዶ
ነፍሳትን አድነን ምጻትህ ፈጥኖ
መሄድ እንሻለን አንተን አጅበን
ይህ ሁሉ እንዲሆን ፈቃድህ ይሁን