ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #68 / Song #68

ሥራው የእግ/ር ነው እኛ ምን እናድርግ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ዳግም ይመለሳል የታረደው በግ
ዋዜማ ደረሰ የበጉ ሠርግ
ነፍሳትን ሰብስበን በቤቱ እናድርግ
1.
የሥራ ጊዜ ወቅቱን አሁን አውቀን
ተነስተን እንሥራ ምፃቱ ይፋጠን
ቤቱ ተሰርቶ ነፍሳት ይዳኑበት
ክብሩ ይገለጥ የሰማዩ መንግሥት
2.
እኛ ተወካዮች ምን እየሠራን ነው
ተኝተን እንደሆን ወዮ ጥፋት ነው
ጊዜ ተሰጥቶን ወንጌል እንድንሠራ
ዘመን ተቆጠረ ሥራው ሳይሰራ
3.
እንሥራ ተነስተን በፍቅር በአንድነት
ቶሎ እንድትመጣ የሠላም መንግሥት
ሲፈርስ እያየን የእግ/ር ቤት
እንዴት እንመልከት በቸልተኝነት
4.
የላከኝን ሥራ ማድረግ ይገባኛል
ድርሻዬን ስወጣ ሥራውም ያልቃል
የመከሩ ጌታ ማጭዱን ይሰዳል
አጭርንም ሥራ በምድር ያደርጋል
100%
100%