1.
ሳይሳሱ ከአገር አውጥተው ውርደት አለበሱህ
ስለፈወስክ አቁስለው በፍቅርህ የጠሉህ
የድሃ አዛኝ የሆንኸው አንተ ነህ ኢየሱስ
ይገባህ ነበር ወይ? ለእኔ አፈር ልትለብስ?
የእግዚአብሔር በግ የሆንኸው
ልቤን በፍቅርህ ያበስኸው
ጓዴ ኢየሱስ እስኪ ና!
የማዋይህ አለኝ ና!
2.
አንተ ፍቅር ነህና ልትጠላኝ አቃተህ
ነፍሴን ከእሣት አወጣህ እራስህን ጐድተህ
የእኔ የሆነ ምን አለኝ? እራሴም የአንተው ነኝ
ስለዚህ ጌታዬ ሆይ! ደጋግመህ ለውጠኝ
3.
ኑሮዬና ተግባሬ ለእኔ ባይጥመኝም
ጠላት እግሬን እየወጋ ቢያደናቅፈኝም
አንድ ጊዜ ቆርጬ ተከትዬሃለሁ
ድካም እንኳ ቢያጠቃኝ እከተልሃለሁ
4.
ያ የምድር ጨለማ አይሎ እንዳይውጠኝ
መንፈስ ቅዱስ ጌታዬ ሳጠፋ ገስጸኝ
መንበርከክን የወዳል ሥጋ ላለም ነገር
ጽናትህን እሻለሁ ከቶ እንዳልቀየር