1.
የኃያላን ኃያል ንጉሥ የሆንከው
ብርሃንን እንደልብስ የተላበስከው
ሁሉም በዙፋንህ ስር ይወድቁልሃል
ኃይለኛው እግዚአብሔር ብለው ይጠሩሃል
ጥንትም ያለህ ዛሬም ያለህ
ወደፊትም ትኖራለህ ባኃይል በግርማ ታበራለህ
ትከብራለህ ትገናለህ ትደምቃለህ ከፍ ትላለህ
ኃይልህን ለብሰህ በዙፋንህ ትጸናለህ
2.
ሊውጠን ተነስቶ እንደሚያገሳ አንበሳ
የጠላት ሠራዊት እልፍ ሆኖ ተነሳ
ሰልፉን ድል አድራጊ የአርያም እሳት
ፈጥኖ ደረሰልን ኢየሱስ የእኛ አባት
3.
ዘመናት ሲያልፉ ታሪክ ሲለዋወጥ
በዙፋኑ አርፎ ጸንቶ የሚቀመጥ
የተዘጋውን ማኅተም ብቻውን የፈታ
የናዝሬቱ ኢየሱስ የጌቶቹ ጌታ
4.
ጠቢቡን ኃያሉን ማንንም ሳይፈራ
የጽድቅ ስራውን በዓለም የሚሰራ
ሃኪም ያልቻለውን በሽታ ሚፈውስ
ኢየሱስ አይደለም ወይ የዓለም ሁሉ ንጉሥ
5.
ኢየሱስ በዓለም ሁሉ ላይ ታወቀ
ዝናውም ገነነ ሄደ እየደመቀ
እናንተ አጋንንቶች ምን ሊውጣቹህ ነው
ሂዱ ተቃጠሉ ስፍራቹህ ጥልቁ ነው