ጌታ ያረገው ሥራ ለእኔስ ገረመኝ
እንደእኔ ማነው ጌታ የደረሰለት ሰው
ይነሳና ያምልከው ማነው ዝም ያሰኘው
1.
የዚች የምድራችን ውበት ሆነ ሀብት
ድሎት ማጣት ሆነ እንዲሁ ማግኘት
አይለየኝም እኔን ከዚህ ከቸር አምላክ
ደስ እያለኝ ሁሌ ጠዋት ማታ ላምልክ
2.
ለጠየቁት ሁሉ ምላሽ ሳያዘገይ
መልስ ይዞ ይቀድመኛል የኔ ጌታ ኤልሻዳይ
ሌላ ማን አለኝ እንዲህ ፈጥኖ ደራሽ
ደስታን አትረፍርፎ እንባዬንም አባሽ
3.
ሁሉን ነገር ተራ በተራ ላውራ ብል
ቃል አጠረብኝ አልበቃ አለኝ
ወደ ፍጥረታቱ ዞር ብዬ ሳያቸው
ሥራው ይገርመኛል አፈጣጠራቸው
4.
ምሥጋናና ክብር ለኢየሱስ ጌታዬ
አቀርባለሁ ዛሬ ይኸው በፊናዬ
በእኔ የጀመረውን ይህን ታምራቱን
መች በዚህ ያበቃል ጌታ እረኝነቱን
5.
የልቤን በደል አይቶ ቢሆን ጌታ
አይሰማኝም ነበር ፀሎቴን ባንድ አፍታ
ምህረቱን ደግሞ አላራቀምና
አመሠግናለሁ ዛሬም እንደገና/2X/
6.
አምላኬ ታጋሽ ነው ሁሉም ይቻለዋል
እንደኃጢያት አይከፍል መቼ ይቸኩላል
ፈጥኖ መለሰልኝ የልቤን መሻት እስከዘለአለም ክብር ይሁንለት/2X/
7.
በጨነቀኝ ጊዜ እግ/ርን ጠራሁ
ዓይኖቼን አንስቼ ወደ አምላኬ ጮሁ
ከመቅደሱ ቃሌን በጆሮቹ ሰማ
እንደሰው አይደለም ይድረሰው ምሥጋና/2X/
8.
ወደአንተ ለሚቀርብ አንተን ለሚጠጋ
መልስ ነህ ኢየሱስ የለም የሚያሰጋ
ምህረቱ አያልቅም ፈጥኖ ይደርስልኛል
ጌታ ሁሉን ቻይ ነው መቼ ይጨክናል/2X/
9.
ሰው ቢሆን ኖር ግን ቶሎ ያጠፋ ነበር
አንተ ግን ታጋሽ ነህ በእምነት ለሚቀርብ
ስለዚህ ልትጋ ልቤን ልክፈትለት
በሁለንተናዬ እርሱ ይንገስበት/2X/
10.
መንገድህን ለጌታ አደራ ብትሰጠው
ለርሱም ብትገዛ ተስፋ ብታደርገው
የልብህን መሻት ምኞት ይፈጽማል
እስከመጨረሻ በድል ያቆምሃል/2X/