ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #108d / Song #108d

ኑ ለእግዚአብሔር ምስጋና እንሰዋ (2)

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: ቤቴል መካነ ኢየሱስ ቤ/ክ «ሀ» መዘምራን
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
ኑ ለእግዚአብሔር ምስጋና እንሰዋ (2)
እርሱ ታላቅ አምላክ ነውና
ምሕረቱ እጅግ እጅግ ብዙ ነውና
1.
ምን ይሳነዋል ጌታ አምላካችን
ሁሉን ሊለውጥ ሊያሳየን ክብሩን
የወደቀውን ያነሣልና
ስለዚህ ለእርሱ ክብር ምስጋና።
2.
ከአዕምሮ በላይ በጣም ታላቅ ነው
የእግዚአብሔር ሥራ የሚደነቅ ነው
መንገዱ ረዊቅ ሥራውም ፍጹም
በሰዎች ሐሳብ የማይታለም
3.
ኑ በአንድነት ምስጋና እንሰዋ
እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ነውና
በጠላትም ፊት ዘይት የሚቀባ-
የድሆች አምላክ የሚያብስ ዕንባ.
4.
የእርሱን ስም ጠርቶ ያፈረ የለም
ኃያሉ ንጉሥ ይክበር ዘላለም
አልፋ ኦሜጋ እርሱ ብቻ ነው
የማይለወጥ ጽኑ ብርቱ ነው
100%
100%