አሻግረን አሻግረን በሰላም ይህን ዘመን
ምህረት ቸርነትህ ፀጋህም ይብዛልን
ከቶ አትለየን አምላካችን
1.
ይህ ፈታኙን ጊዜ በሠላም አሻግረን
እምነታችን ሳንተው ይልቅ እየፀናን
ትዕግሥት የሚነሳ ዛቻ ቢያይልብን
የሚያስችለን ፀጋ የሱስ ስጠን
2.
የማያምን ትውልድ በቅናት ተነሱብን
እውነትን ለማጥፋት በኃይል ተሰለፉብን
ክፉ አመንዝራ ትውልድ ከአፍ ተንኮል ብቻ
ምንም ሰላም የለም ሁሌ ዛቻ
3.
በእያንዳንዱ ፊት በዝቷል ክፉ ንዴት
ክህደት አመፅ ሞልቶ በአንደበት ሀሰት
ይህን ክፉ ዘመን በሠላም አሸግረን
ልብሳችንም ሳይረክስ የእምነታችን
4.
ይህ መከራን ዘመን በሠላም አሻግረን
የብርሃንን ጮራ ውበት እንደ ያዝን
በእውነት ላይ ቆመን ድካም ሳይኖርብን
የሠማይን ደጃፍ ጌታ አድርሰን