ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #62 / Song #62

ዘመኑን አይተህ ዋጀው

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
የሱስን አውቀህ እመነው
ያለዚያ ህይወት ጠፊ ነው
ጌታህን ዛሬ ምረጠው
1.
ለዓለም ኑሮ መሮጥህ
ቀንና ማታ መልፋትህ
እረፍት ማጣት ስቃይ ነው
ጐዳቱ ዞሮ ያንተ ነው
2.
ለእንጀራ ጌታ መጣሉ
የሱስን ጐኑን ማቁሰሉ
ሚስጥሩን ሳታውቅ ቀርተህ ነው
ያለኸው በርሱ ህይወት ነው
3.
የዓለም ምኞቱ ያልፋል
ያማረ ሁሉ ይቀራል
ያኔ ነው መግቢያ ማጣቱ
የሱስን ያጣ በህይወቱ
4.
ወገኔ እስቲ ንገረኝ
ያለምን ጥቅም አሳየኝ
ተመለስ ጌታ ይሻልሃል
ኑሮህን እርሱ ያቀናል
5.
እምነትህ ለምን ይጐላል
አምላክህ ሁሉን ያደርጋል
እምነትን ማጣት መጉደል ነው
ማመኑ ለእኛ ማትረፍ ነው
100%
100%