1.
ከምድረ በዳው ኑሮ ከዚያ ከቃጠሎ
አንተ ነህ የታደግሃት ደረስክላት ቶሎ
ስለዚህም ነፍሴ አንተን አንተን አለች
ቀንና ሌሊት ፊትህን ፈለገች
ዋላ ወደውኃ ምንጭ እንደምትናፍቅ
ነፊሴ አንተን አንተን አለች (2)
2.
ኢየሱስ አንተ ነህ ለነፍሴ ትርጉሟ
እውነተኛ ወዳጅ የኑሮ ጣዕሟ
ያላንተ መኖር ከቶ አይሆንላትም
መጠጊያ ጐጆ ሌላ የላትም
3.
ባስለመድከኝ ስፍራ እጠብቅሃለሁ
አንተን ካላገኘሁ መቼ እተኛለሁ
ሌሊት ጭር ብሏል ሰው ሁሉ ተኝቷል
ከአንተ ጋር መሆኑን ነፍሴ ግን አምሯታል
4.
እግዚአብሔር አለቴ እመካበታለሁኝ
እስከ ዘለዓለሙ ተስፋ አደርጋለሁኝ
ምንም ሳትሰራልህ ነፊሴን ወደሃታል
ለቀሪውስ ጉዞ ምንድን ያሰጋታል