ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #208d / Song #208d

ቀንዴ ከፍ ከፍ አለ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
1.
ኑሮዬ ያልተሳካልኝ ዕድለ ቢስ ነኝ እኔ
እያልኩኝ እኖር ነበር በዚህች ሕይወት ዘመኔ
ዛሬ ግን በኢየሱስ ከፍ ከፍ ብሎ ቀንዴ
በምሥጋና ተሞላሁ አልፎ የችግር ዘመኔ
ቀንዴ ከፍ ከፍ አለ (፪x)
አፌም በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ
ልቤም በእግዚአብሔር ጸና (2)
እስኪ ቆሜ ለጌታዬ ልሰዋ ምሥጋና (2)
2.
የዕለት ምግቤን እንኳን ከሰው እየጠበኩኝ
ሰዎችን ተስፋ ሳደርግ በልመና ወደኩኝ
ዛሬ ግን በኢየሱስ ከፍ ከፍ ብሎ ቀንዴ
ጐተራው ሁሉ ሞልቷል ረሃብ ጠፍቷል ከሆዴ
3.
አንገቴን አቀርቅሬ ተደፍቼ ሄጃለሁ
ደግሞ ለጠላቶቼ መሳለቂያ ሆኛለሁ
ዛሬ ግን በኢየሱስ ከፍ ከፍ ብሎ ቀንዴ
ቀና ብዬ ተራመድኩኝ ተከፈተልኝ አፌ
4.
ለቅሶዬን ወደ ደስታ ጩኸቴን ወደ ሆታ
ማቄንም ባማረ ልብስ ለውጦልኛል ጌታ
ዛረ ግን በኢየሱስ ከፍ ከፍ ብሎ ቀንዴ
ሁሉ ነገር አልፏል ይክበር መድሃኒቴ
100%
100%