ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #272d / Song #272d

ነፍሴን በፊትህ አፈሳለሁ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: ታምራት ኃይሌ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
ነፍሴን በፊትህ አፈሳለሁ
እጄን ወደ አንተ አነሳለሁ
ከመቀመጫዬ እወርዳለሁ
ከእግሮችህ በታች እሰግዳለሁ
አምላክ ነህና አመልክሃለሁ
ንጉሥ ነህና አነግሻለሁ (2)
1.
ሊታይ በማይችል ብርሃን ውስጥ አለህ
ሰማይ ምድርን በቃል ታዛለህ
ወደም ጠላም ፍጥርት በሙሉ
ይገዛልሃል የአንተ ነው ኃይሉ
2.
ሰው ህልውናው ሞትና ሕይወቱ
ሃዘን ደስታው ሹመት ሽረቱ
ትዕዛዝ ሁሉ ከአንተ ይወጣል
ክብር ላንተ እንጂ ለማን ይሰጣል
3.
እስከ እግርህ ጣት ዕንቁ ለብሰሃል
ወገብህንም በወርቅ ታጥቀሃል
ራሽ ነጭ ነው ዐይንህ ነበልባል
ክብርም ስግደትም ለአንተ ይገባሃል
4.
እግርህ በእቶን የነጠረ ናስ
ድምጽህ ያስፈራል እንደውቅያኖስ
የተሳለ ሰይፍ ከአፍህ ይወጣል
ከቀትር ፀሐይ ይልቅ: ፊትህ ያበራል
5.
ውለታህ በዝቶ ቢያስጨንቀኝ
ያለኝን ሸጬ ሽቶ ገዛሁልህ
ብልቃጡ ይሰበር ይፍሰስ በእግርህ
እንዳከበርከኝ እኔም ላክብርህ
100%
100%