ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #2d / Song #2d

አሜን ምስጋና

Amen Praise to God

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: ተመስገን
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 21
አሜን ምስጋና/2/ በእልልታ
የማታ ማታ ድሉ የጌታ
የማታ ማታ ድሉ የኛ የጌታ
1.
ጠላት ተመታ አንክሶ
የታለ ዛሬ የትላንቱ ለቅሶ
በ ኢየሱስ ታብሶ ታብሶ (4)
2.
ጠላት ወደቀ ተረቶ
በስሙ ስልጣን በብርቱ ተወግቶ
በ ኢየሱስ ተረቶ ተረቶ (4)
3.
ቀናት ቢቆዩም ቢረዝሙም
ከለመነው አንድም አልጎደለም
ዛሬ አየን ሁሉንም ሁሉንም (4)
4.
የአምላክ ምህረቱ ብዙ ነው
ጥበቃው ፍቅሩ ከአእምሮ በላይ ነው
ይኸው ሰው አረገን ይመስገን (4)
100%
100%