ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #40 / Song #40

ከጨለማ የተነሣ በሥራት መናገር

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ሥጋችን አዋርደን ስምህን ማስከበር
አናውቅምና ጌታ አንተን መጠበቅ
ጌታ አንተ አስታውቀን የምንለውን /4/
1.
ባልታጠቡ እግሮች በፊትህ ቁመናል
የኃጢያትን ጫማ በግራችን አርገናል
ባልፀደቀው አፋችን እንዘምራለን
ስለስምህ ብለህ ፀጋህን አብዛልን
2.
አይናችን እያየ መመልከት አንችልም
ድምፅህን እየሰማን ማስተዋል አቃተን
ብንጮህ ብንጮህ አንተ ካልባረከን
ከንቱ ልፋት እንጂ ትርጉም አይሰጠንም
3.
ሥጋ በመሆናችን መልካም ነገር የለም
ከእኛ የሚጠበቅ አንዳች አይገኝም
ስለዚህ ጌታ ሆይ ካንተ እንጠብቃለን
ተናገር ያልከውን ብቻ እናወራለን
4.
ሕይወታችን የመፅሐፍ ቃልህን ሊያረክሰው
ትዕቢትና ትምክህት በስምህ ተፍቀው
ዝናና ክብራችን ባንተ ተሰውሮ
ልናይ እንሻለን አምላካችን ከብሮ
100%
100%