ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #34 / Song #34

ምራን እረኛችን የሱስ ተስፋችን

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ፀንተን እስከምንደርስ በሠማይ ቤታችን
1.
ትርጉም ያለው ኑሮ መኖርን አስተምረን
የሰላሙ ንጉስ ንገስ በሕይወታችን
2.
ውዱ አምላካችን አንተ ነህ መሪያችን
ጥበቃህ አይለየን ሲዝል ጉልበታችን
3.
ሥንፈራ ስንደክም ስንተክዝ ስናዝን
ጌታ ሆይ በመንፈስህ አበርታን አፅናናን
4.
ጠውልገን እንዳንቀር ሙላን በባርኮትህ
አለምልመን በፀጋህ አቁመን ለክብርህ
5.
ከውስጥም ከውጪም ፈተና ሲያጠቃን
አትለየን አንባችን የሱስ እረኛችን
100%
100%