ማየቱንም አየን የሱስ መመልከት ይኸው ተሳነን
ልባችን ደንድኖ ቀርቶ ማስተዋል ከኛ ራቀ
አባ ባክህን ስማን ስማን እኛን ልጆችህን
ፀጋህን ለእምነት ጥበብን ለእውቀት
ኃይልን ለብርታት ስጠን ጌታ እንለምንሃለን
1.
ዘመኑ ቀርቧል ብለን አቤት ስንናገር
አጋንንት ያባራል ቅኔያችን ስንዘምር
ቢሆንም ጌታ እኛ መለወጥ ርቆናል
ለካስ አለወቅንም እውነትን ክደናል
እሬትን ደብቀን ማር ማጥፋት ይዘናል
እባክህ ቅረበን ጊዜው አስግቶናል
2.
ቃሉንም ለማንበብ እጅግ አዋቂ ነን
በትንቢት ስጦታ አይወዳደሩን
አልተመለከትንም ለካስ ታውረናል
ተበጥረን ልናርፍ እዳር ላይ ደርሰናል
በስም ጽድቅን ለብሰን ኩነኔን ይዘናል
ጌታ ድረስልን ፀጋህ ሽቶናል
3.
ከባቢሎን ውጡ ስንል ቆይተናል
የመዳንን ብሥራት ለዓለም ተናግረናል
አንተን እንደምናውቅ በድፍረት ብለናል
ነገር ግን ውስጣችን በእኔነት ተውጧል
እጅግም አዝነናል ሥጋችን አምጾ
ስለዚህ ለመንህ ከኛ ኃይል ተሟጦ