ራሴን ልመልከተው አጥርቼ ሌላውን ትቼ
ዓይኔን ወደ አንተ መልሰው አንሳልኝ ከሰው።
1.
ኧረ እባካችሁ ስዎች አንድ በሉ
አየኔ ሰውን ሊያይ ምነው መቸኮሉ
ፍሬ የሞላው ወይን እየሱስ እያለ
ሸንበቆን ለማየት አይኔ ኮበለለ
2.
የስዎችን ጉድለት አንድ ሁለት እያሉ
አይጠቅምም በወሬ ጊዜ ማቃጠሉ
የሌላውን ጉድፍ ማየት ይቻለኝ ዘንድ
ትልቁ ምሰሶ ከእኔ አይን ይወገድ
3.
አጠፋ ለራሱ አበጀ ለራሱ
ሁሉም ለፍርድ ቀን ይዘጋጅ ለመልሱ
እኔም ከእንግዲህ አይኔን ቀጥቻለሁ
ከሰው ላይ ነቅዬ ወዳንተ አንስቻለሁ።
4.
ሁለመናህ ንጹህ እንከን የሌለብህ
ቅንጣት ያህል ጉድፍ የማይገኝብህ
አንተን ማየት ቢችል አይኔ ተስተካክሎ
ጠላት ባልሳቀብኝ ነፍሴን አጎሳቁሎ።