ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #130d / Song #130d

ምስጋና አይጓደልብህ የተገባህ ስለሆነ የተገባህ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: ሰሜን አዲስ አበባ መሠረተ ክርስቶስ ቤ/ክ ሀ-መዘምራን
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
ምስጋና አይጓደልብህ የተገባህ ስለሆነ የተገባህ
ምስጋና አይጓደልብህ ገዝተትኸኛል ጌታ
እኔንም በፍቅርህ።(2)
1.
ባለታላቅ ገናና ሞገስ ያለህ
ማን ይቆማል በድፍረት ከአጠገብህ
እኛ ግን እናይሐለን በውበትህ
በዝቶልን ምሕረትህ።(2)
2.
ልትከበር ይገባሃል ቸር አምላክነህ
ቀንና ሌት ምሥጋና ይቅረብልህ
ልጆቼ ብለህ ጠራሥኽኸን አከበርከን
ወዳንተ አቀረብከን።(2)
3.
ኃጢአትን ምትቆጥር ብትሆንኖሮ
መልካም ነገር አይገኝም በኛ ኑሮ
ይቅርታህ ግን በዝቶልን አልጠፋንም
ከእቅፍህ አልወጣንም።(2)
4.
በልጅህ ደም ገዝተኸን አፀደቅከን
በመንፈስህ አትመህ አስጠጋኸን
ዛሬም ከአንተ ፊት አለን
በመቅደስህ ስመሃን።(2)
100%
100%