1.
ለዚህ ዓለም ባዕድ ሆነን
ኢየሱስን እንጠብቃለን
እዚህ ዛላቂ ቤት የለንም
እርስታችን በሰማይ ቤት ነው
ቤታችን ፈራሽ ድንኳን ነው
እስክንሄድ ከዚች ዓለም
እዚህ ነዋሪ ቤት የለንም
እርስታችን በሰማይ ቤት ነው
2.
በመከራ በስደትም
አናምርር አናጉረምርም
ለአጭር ጊዜ እንቆያለን
ኢየሱስ መጥቶ እስኪወስደን
3.
በአዲሲቷ ኢየሩሳሌም
እንግዶች በማንሆንበት
ከጌታ ጋር ባለእርስቶች
የተገዛን የአምላክ ልጆች
4.
የግብጻውያንን አገር ትተው
እንደወጡ እስራኤላውያን
እንገሥግስ እኛም ወደፊት
ወደ ሰማይ የተስፋ ርስት