ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #320d / Song #320d

በሰማይ ዙፋን የተቀመጠ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
በሰማይ ዙፋን የተቀመጠ
በእግሩ ምድርን የረገጠ
የሰማይ የምድር ፈጣሪ
ለዘለአለም ነዋሪ
አይገረሰስም ዙፋኑ
ማንም አይሽረውም ስልጣኑን
የርሱ ልጆች ነን ሁላችን
እጥፍ ድርብ ነው ደስታችን
1.
የሰማይን አምላክ መንግስት የምንወርስ
ዘላለም ከርሱ ጋር አንረን የምንነግስ
የተወለድን ነን ከማይጠፋ ዘር
አባታችን ሆኗል ሕያው እግዚአብሔር
2.
የወንጌል የምስራች ይነገር በይፋ
ሲኦል ባዶ ይሁን የአምላክ መንግስት ይስፋ
የመስቀሉ ጠላት ይንደደ እንዳመሉ
እግዚአብሔር ይክበር አሜን እልል በሉ
3.
ወይኑ ክርስቶስ ነው ገበሬ አባቱ
እኛም ቅርንጫፎች የአካል ብልቱ
ሳይጣን እንደገፋን ሰውም እንደጠላን
አለምን በሙሉ በፍሬያችን ሞላን
4.
ቀንበሩ ልዝብ ነው ሸክሙ ቀሊል ነው
አገዛዙ በፍቅር መመሪያው ግልጽ ነው
በዘመናት ሁሉ ኃያል የድል ጌታ
100%
100%