አትለየን አንተ አትለየን
በዚች ዓለም ኑሮ ብቻችንን
አትተወን የሱስ እባክህን
1.
እኛ ደካሞች ነን ካንተ በቀር
መውጣት አንችልም ካለም ነገር
እርዳታን ካንተ ዘንድ እንሻለን
ወዳጃችን የሱስ ቶሎ ናልን
2.
እጃችንን ያዘን እንላለን
እኛ ከያዝንህ ግን እንለቅሃለን
ሚያበረታው መንፈስህን ላክና
እንድንቆም እርዳን እንደገና
3.
ዛሬ በአንድ ልብ ለመሆን
ጭራሽ አቅቶናል ሁላችን
አንድ አድራጊው የሱስ ቶሎ ድረስ
የመሠረትከው ቤት ሳይፈራርስ
4.
ፈቃድህ በምድር ላይ ይሁንና
ኃጢያታችንን ይቅር በለንና
ልጆችህ አድርገን ለአንተ ክብር
ለዘላለም ጠላታችን ይፈር