ላመስግንህ ጌታ ላመስግንህ
ለእኔ ስላረከው ብዙ ስራህ
እንዲያው ቢሆንልኝ ለውለታህ
ላመስግንህ ላመስግንህ
1.
የተረሳሁ ነበርኩ የተጣልኩኝ
ውዴ ኢየሱስ አንተ ባትፈልገኝ
ከጉድፍ ከአመድ አንስተኸኝ
ከቅዱሳንህ ጋር አከበርከኝ (ላመስግንህ)
2.
በዐይን የሚሞሉ ታላላቆች
እያሉ የከበሩ ብዙ ሰዎች
ነፍስ ዘርተህብኝ የሞትኩትን
አገልጋይ አደረከኝ ለአንተ የማጥን (ላመስግንህ)
3.
ጌታ ትገድላለህ ታድናለህ
ሲኦል ታወርዳለህ ታወጣለህ
ድሃ ታደርጋለህ ባለፀጋ
ሐሳብህን የለም የሚከለክል (ላመስግንህ)
4.
ልቤ በአንተ ጸንቷል መድሃኒቴ
አፌም ተከፈተና በጠላቴ
ደስ ብሎኛልና በማዳንህ
ሞገስ ይሁን ለአንተ ይስፋ ክብርህ (ላመስግንህ)
5.
አምላኬ ሰው ሆንኩኝ በአንተ ስራ
ጠዋት ማታ ስምህን የምጠራ
ኢየሱስ በመቅደስህ በማደሪያህ
ምሥጋናዬ ይድረስ ወደፊትህ (ላመስግንህ)