ይህ ቤት ያንተ ነው ሥፍራውም ያንተ ነው
እኛም ያንተው ነን ጊዜውም ያንተው ነው
ሁሉን ሰጥተንሃል ደስ እንዳሰኘህ አድርገው። (2)
1.
ፈውስ የሚያስፈልገው ሀመምተኛው አለ
በዲያብሎስ ውጊያ ልቡ የቆሰለ
ያለውን አራግፎ ባዶውን የመጣ
ካንት የሚጠቅ ስለማይታጣ
በባሪያዎችህ አፍ በረከትህ ይፍስስ
ጌታ በዚህ መሐል ክብርህ ይመላለስ (2)
2.
በሰለሞን መቅደስ ታቦትህ ባለበት
የክብር መንፈስህ እንዲፈስስበት
ደግሞም በደመና ዙሪያውን እንዳጠርክ
ዛሬም በዚያ ኃይልህ ይህን ቤት ባርከው
በዘርፋፋ ልብስህ ግባ እለፍበት
ዛሬም በዚህ ቤት ኃይልህ ይረፍበት (2)
3.
የቀራንዮ ፍቅርህ ጠርቶ ሰብስቦናል
በዚሀ ልንከማች ምክንያት ሆኖናል
ጌታ ሆይ አንተ እንጂ ሰው አይናገረን
የሁላችን አይን ወዳንተ ነውና
አጽናናን በቃልህ ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና (2)