ተገናኘን የሱስ ሆይ ተገናኘን
ተገናኘን መንፈስ ሆይ ተገናኘን
ባዶ ማድጊያዎች ነን ዘይት የሌለን
1.
እስካሁን በደረቅ ኑሮ ኖረናል
ዝናብ ያስፈልገናል ጠውልገናል
ድካም እንዳያገኘን በጐዞአችን
ያንተው መንፈስ ይሥራ በዘመናችን
2.
በቤትህ እጅግ ዓመት ቆይተናል
ዕድሜን በመቁጠር ብቻ አርጅተናል
ኧረ ማረን ብለናል እባክህ
በእኛ ውስጥ ይደር ይዋል መንፈስህ
3.
የጥንቱን እምነትና ፍቅር ስጠን
መሀሪ ነህና በምህረትህ እየን
ይህን ያህል ቆይተን እንዳንጠፋ
በሙላት ተገናኘን የኛ ተስፋ
4.
ባዶ ማድጋዎች ነን ዘይት የሌለን
ቀላል ንፋስ ቢመጣ የሚጥለን
የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ አቤቱ
እንደገና መስርተን በአለቱ