ኦ ግሩም ኃይል ነው(2)
ጌታዬ ሆይ በክንድህ ውስጥ ያለው
ኦ ግሩም ኃይል ነው
1.
ፀሐይ ከዋክብትን በአየር አንሳፈሃል
መሬትን በድምቀት በውበት ፈጥረሃል
ነፋስን በምድር ላይ እንዲኖር አዘሃል
ክበር ጌታዬ ሆይ ክቡር ኃይል ለብሰሃል
2.
ለአበቦች መዓዛን ለእንስሳት ማደሪያን
ለወፎች ጐጆ ለአራዊት ጫካን
ለዓሣ ባሕርን መኖሪያ አድርገሃል
ክበር ጌታዬ ሆይ ክቡር ኃይል ይዘሃል
3.
ተራራ ሸንተረር ወንዙን ሜዳውንም
ፈጥረሃል ጌታ ሆይ የሚሳንህ የለም
ጥበብን ለሰው ልጅ በምድር ላይ ሰጥተሃል
ክበር ጌታዬ ሆይ ክቡር ኃይል ይዘሃል