ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #60d / Song #60d

አሽናፊ ነው ጌታዬ ኢየሱስ

English translation

ምድብ / Category: ስግደት / Worship
ደራሲ / Author: Unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 5
አሽናፊ ነው ጌታዬ ኢየሱስ
አሸናፊ ነው ጌታዬ ኢየሱስ (2)
ሁሉን ይረታል ኤልሻዳይ ነው (2)
1.
የፅዮን አምባ የነፍሴ ንጉሥ
መች ትመጣለህ እስከዚያው ልታገሥ
የበጉ ሠርግም ተዘጋጅቶላታል
ነፍሴ ልትከብር ጥቂት ቀን ቀርቷታል
2.
ዘመድ ቢከፋ ቀናት ቢለወጡም
ወዳጅ ዘመድም ባንድነት ቢከዱም
አንተን አመልካለሁ ብቻ እኔን አቁመኝ
ጐርፍ እንዳይወስደኝ በፀጋህ ደግፈኝ
3.
በሕይወቴ ታይ ግለጽ ክንድህን
ፀጋህ ይትረፍረፍ አፍስስ ኃይልህን
በድንቅ በተዓምር ይታወቅ ስምህ
ለሕዝቡ ይገለጥ ያ ገናናው ክብርህ
4.
በክንድህ አቅፈህ ለዘለዓለም ልረፍ
በቃህ መከራ ዓለምን አሸነፍህ
የሚል ድምጽህን መቼ እሰማለሁ?
እስክትመጣልኝ እጠብቅሃለሁ
100%
100%