ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #26h / Song #26h

አምላክ ይመስገን

Revive us Again

ምድብ / Category: ስግደት / Worship
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 4
1.
አምላክ ይመስገን
ልጁን ስለሰጠን
በክቡር ደሙ ደግሞ
ስለ ገዛን
ሃሌሉያ ክብር ላንተ
ሃሌሉያ አሜን
ሃሌሉያ ክብር ላንተ
አድሰን አሁን
2.
አምላክ ይመስገን
መንፈስ ስለሰጠን
ከጨለማ ወደ ብርሃን
ስለመራን
3.
ክብር ምስጋናም
ለክርስቶስ ይሁን
ከኃጢዓታችን ፈጽሞ
ስላነጻን
4.
ክብር ምስጋናም
ላምላካችን ይሁን
አንድ ልጁንም
አሣልፎ ለሰጠን
5.
አድሰን አሁን
ፍቅርህን አካፍለን
ከሰማይም መንፈስህን
አውርድልን
100%
100%