ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #150d / Song #150d

ያ ነው ደስታዬ

English translation

ምድብ / Category: ስግደት / Worship
ደራሲ / Author: Unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 4
ያ ነው ደስታዬ
ያ ነው ተስፋዬ
ጌታዬን ሳየው ለብቻዬ (2)
1.
መፃተኛ ነኝ በዚህ ምድር ላይ
የንጉሥ ልጅ ነኝ አገሬም በሰማይ
አምላክ በክንፉ ይጋርደኛል
ከቀትር ጋኔን ይሰውረኛል
2.
መልካም ዘር ዘራ ጌታ በማሣው
እንክርዳድ ግን ገብቶ አበላሸው
አዳዲስ ነገር ጌታ አስተምረኝ
ለሰይጣን ዘዴ ብልህ አድርገኝ
3.
በምድር ገጽ ሁሉ እንዲያስከብሩህ
ፀጋህን አብዛ ለአገልጋዮችህ
በድካማቸው ራራላቸው
አገልጋዮችህ ብዙዎች ናቸው
100%
100%