ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #4d / Song #4d

እጅ ለእጃችን

Holding hand in hand

ምድብ / Category: ስግደት / Worship
ደራሲ / Author: temesgen
👁️ Views: 10
እጅ ለእጃችን ተያይዘን
ኢየሩሳሌም እንገባለን
በኢየሱስ ደም አንድ ሆነናል
አንለያይም ተዋደናል ።
1.
መልክና ጐሳ ደም ግባት እውቀት
ከቶ አይለየንም ከያዝነው እምነት
በቀራኒዮ በፈሰሰው ደም
ከእንግዲህ አንድ ነን ሰይጣንም ይፈር።
2.
በመሃላችን ገደብ አይኖርም
አጥር ግድግዳ አይሠራም ማንም
የኢየሱስ ደም አንድ አድርጐናል
እንዘምራለን ሃሌ ሉያ እያልን ።
3.
ታላቅም ታናሽ ክፉ ጨዋ የለም
ሁሉ አንድ ሆኗል በክርስቶስ መስቅል
ኣባትና ልጅ አንድ እንደሆኑ
እኛም አንድ ሆንን ሲወርድ መንፈሱ።
4.
እንደመልካችን የሁሉ ጠባይ
ሁሌ አንድ ባይሆን ምንም ቢለያይ
ግን በውስጣችን የያዝነው ጌታ
እርሱ አንድ ነው አንድነን በቃ።
5.
የእግዚአብሔርን ሥራ እንሠራለን
እርስ በርሳችን አንድ ልብ ሆነን
በፍጹም የልም የሚያግደን
የመንፈስ ቅዱስ ችቦን አንድደን።
100%
100%