ልናርፍ ነው ፣ ወንድም
ልናርፍ ነው
ኢየሱስ ሊመጣ ሊወስደን ነው (፪X)
1.
መለከት ሊነፋ መላዕክቱን ሊያዝዝ ነው
የልጆቹን ነገር አላስችል እያለው
ጌታችን ይመጣል ከጽዮን ተራራ
ልንሄድ ነው እኛም ልንኖር ከእርሱ ጋራ
2.
መሯሯጥ መባከን ይኸ ሁሉ ያበቃል
የሚያስፈልገንን ኢየሱስ አዘጋጅቷል
ዓይናችን ተከፍቶ ጌታን ልናይ ነው
እጆቹን ዘርግቶ እኛን ሊቀበለን ነው
3.
እንበርታ እንጽና እንባችንን እንዋጠው
ተስፋችን ሊመጣ ሊያሳርፈን ነው
ኢየሱስ ሊመጣ ነው ከመላዕክቱ ጋራ
ልናርፍ ነው እኛም ከዚህ ዓለም መከራ